ከሃምሳ ዓመት በፊት በሸኽ ሙሐመድ ሳኒ ሃቢብ እና ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ የቀረበው የክቡር ቅዱስ ቁርኣን የአማርኛ ትርጉም፤ እንሆ በወንድም ሙሐመድ ፈረጅ ድምፅ ተዘጋጅቶ በተለያዩ የቅዱስ ቁርኣንን ትርጉም ማድመጥ ለሚፈልጉ አመቺ ኾኖ ቀርቧል።
የድምፅ ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርቡ በዚህ መተግበሪያ እስኪጫን ለጊዜው ሱረት አል ፋቲሃን ጨምሮ ከሱረቱ አን እስከ ሱረቱ አን ነበእ (አንድ ጁዝ) የትርጉም ድምፅ ሥራው ያለክፍያ ቀርቧል።
በዚህ አጋጣሚ እንደ አላህ ፈቃድ ሥራችንን ከእንከን ለማድረግ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና ጥንቃቄ ጥረት ያደረግን ቢኾንም፤ ሰዎች ነንና ልንሳሳት እንደምንችል እናምናለን። በመኾኑም ይህ ሥራ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር የቅዱስ ትርጉም እንደመኾኑ በማድመጥም ኾነ በማንበብ ውስጥ የሚታያችኹን ክፍተት እንድተጠቁሙን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
ይህን ታላቅ ሥራ አኑረው ያለፉ አባቶቻችንንና ከህትመት ስርጭት የደከሙ ወንድምና እህቶችን ኹሉ ለሠሩት መልካም ሠራ ምንዳውን ያብዛላቸው። እኛንም በሰማነው የምንጠቀም ያድርገን። አሚን!!